Wednesday, 3 April 2013


Thousands of Ethiopians and Eritreans stranded in northern Yemen


(UN Radio) - The voluntary repatriation of thousands of undocumented migrants from Yemen is likely to stall in the next six months due to lack of adequate funding, according to the International Organization for Migration (IOM).

About 3,000 migrants from Ethiopia, Eritrea and Somalia are stranded in the northern Yemen town of Haradh, where living conditions are said to be deteriorating on a daily basis.

IOM says it can only distribute about 300 meals per day mainly to the most vulnerable women, the elderly and unaccompanied minors.

Jumbe Omari Jumbe from IOM says the stranded migrants are extremely vulnerable to human traffickers and criminal gangs dealing in human organs.

"Shelter capacity and medical referrals have also been also reduced, resulting in increased hardship and illnesses among the migrants. Currently, the Haradh hospital mortuary is filled with the unclaimed bodies of migrants. In addition, IOM has suspended its voluntary repatriation programme because of the lack of funds. The last IOM-sponsored flight to carry migrants from Yemen was in September 2012,when 210 migrants were voluntarily repatriated to Ethiopia. In Haradh town, thousands of migrants roam the streets and sleep rough in the open with no money for food or medicine.They include single women, unaccompanied minors, the elderly and the sick – most of whom are desperate to return home."

The number of migrants entering Yemen has more than doubled over the last two years from 53,000 in 2010 to over 107,000 last year.
Source Ethiopian Review.

Tuesday, 2 April 2013


ሰበር ዜና) አርቲስት ቲዎድሮስ ካሳሁን ለጊዜው ምንነቱ ባልታወቀ አለመግባባት ምክንያት ከባለቤቱ መፋታቱ ተነገረ

The recently married artist Tewodros Kassahun aka Tedy Afro has reportedly been divorced, sources closer to the artist Told EthiopianObserver. The divorce comes after a continuous argument between the two. According to the sources Amleset Muche has already left him and now she is with her parents. Our effort to reach Tedy Afro via phone is not successful yet. Read More on EthiopianObserver
በቅርቡ ጋብቻቸውን የፈፀሙት አርቲስት ቲዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና ባለቤቱ መፋታታቸው እየተነገረ ነው፡፡ ለአርቲስቱ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ትናንት ምሽት አካባቢ ለኢትዮጵያን ኦብሰርቨር እንደጠቆሙት ጥንዶቹ የተፋቱት ለቀናት በዘለቀ አለግባባት ምክንያት ነው፡፡ ለጊዜው አለመግባባት የተፈጠረበት ምክንያት ግልፅ ባይሆንም ጉዳዩን አጣርተን እንደደረሰን እናቀርባለለን፡፡ የቴዲ ባለቤት በአሁን ሰዓት በቤተሰቦቿ ቤት እንደምትገኝ ተረጋግጧል፡፡
ጉዳዩ እንዲህ ነው
ያለፉት 13 ቀናት ለአርቲስት ቲዎድሮስ ካሳሁን እና ባለቤቱ አምለሰት ሙጬ ጥሩ አልነበሩም፡፡ ቴዲ በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ጮክ ብሎ ማውራት ጀምሯል፡፡ አምለሰት ባሌቤቷ ቅናት ብጤ እንደጀማመረው እርግጠኛ ሆናለች፡፡ ሁኔታው ቢያስቃትም እየተደጋገመ ሲሄድ ግን ትግስቷ ያለቀ ይመስላል፡፡
“ቢያንስ ቀስ ብለህ አውራ ጎረቤት እስኪሰማ ድረስ ለምን ትጮሃለህ” ስትለው እንደነበርም ግድግዳ ተደግፈው ሲያዳምጡ እንደነበር የሚገልፁ የአርቲስቱ ጎረቤቶች ለኢትዮጵያን ኦብዘርቨር ተናግረዋል፡፡ የመረጃ ምንጮቻችን አያይዘውም ቴዲ ሰሞኑን የማንንም ስልክ እያልመለሰ መሆኑን ነው የጠቆሙት፡፡
አርቲስቱ በቅርቡ “ትዳር” የተሰኘ አልበም ለማውጣት በእንቅስቃሴ ላይ ነው ያሉት እንዚሁ ምንጮቻችን አሁን ከተፈጠረው ሁኔታ አንፃር የዘፈኖቹ ይዘት ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም ባይ ናቸው፡፡
ይህን መረጃ እያጠናከርን ባለlበት ሰዓት አርቲስቱ ቤቱን ቆልፎ ከአዲስ አበባ ራቅ ወዳለ ቦታ ሳይሄድ እንዳልቀረም የሚጠቁሙ መረጃዎች እየደረሱን ነው፡፡ ምናልባትም በአሁን ሰዓት አርቲስቱ ራቅ ወዳለ ቦታ የሄደው ለአዲሱ አልበሙ መጠሪያ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀውን “ትዳር” የተሰኘ ዜማ ለመለማመድ ሳይሆን እንደማይቀር ይህን አፕሪል ዘ ፉል አስቀድመው ነቄ ያሉ ሁላ ይደርሱበታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
እወነታው ይሄ ነው፡፡ ቴዲ አፍሮና ና ተወዳጇ ሚስቱ አሁንም ትዳራቸውን በፍቅር እየመሩ ነው፡፡ የአብርሃምና የሳራ እንዲሆንላቸውም እንመኛለን፡፡
Read More on EthiopianObserver
source freedom4Ethiopian

የግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ አካል ነዉ፣ በሚል ርእስ መግለጫ ያወጣ ሲሆን በመግለጫው ላይ እንዳሰፈረው ወያኔ በዚህ በያዝነዉ አመት ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ  በአማራዉ ህዝብ ላይ አዲስና ሰፋ ያለ የጥቃት ዘመቻ መጀመሩን አውስቱአል፣  የግንቦት ሰባት ንቅናቄ    በዚሁ መግለጫ ማጠቃለያው ላይ በአማራዉ ብሔረሰብ ላይ በማነጣጠር እየተፈጸመ ያለው የማፈናቀልና  የማጥቃት እርምጃ በአገሪቱም ሆነ በአለም አቀፍ ህጎች ሁሉ  በዘረኝነት ወንጀል የሚያስጠይቅ ከፍተኛ  በደል ነው ብሎአል።
የፕሮግራማችን ተከታታዮች የዚህን መግለጫ ሙሉ ቃል ከዜናው በማስከተል የምናቀርብ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።
ይህ በንዲህ እንዳለ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በፍኖተሰላም እና በባህርዳር ከተማ ያለመጠለያ ተበትነው የሚገኙ የአማራ ተወላጆች፣ ለዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ባደሩ ሆድ አደር ባለስልጣናት አሁንም ግፍና በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ አመለከተ። የግንቦት ሰባት ዘጋቢ ከባህር ዳር ባስተላለፈልን በዚሁ ሪፖርት ላይ እንዳመለከተው እነኝህ ተፈናቃዮች እያቀረቡ ላለው ጥያቄ  የክልል ባለስልጣናት ተብየዎች ምንም አይነት መፍትሄ ሊሰጡአቸው ባለመቻሉ ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውንና ከዚህም አልፎ ከህዝብ እይታ ለመሰወር በሚል ራቅ ወዳለ ቦታ እንዲሰፍሩ መደረጋቸውን  ገለጹአል።
ዘጋቢያችን እንደገለጠው እነኝኝህ በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ሰፍረው የነበሩ ከ3 ሺ በላይ ተፈናቃዮች ከመሀል ከተማ እንዲወጡ ተደርገው፣ ጃቢ ጣህናን ወረዳ ውስጥ ባከል እየባለች በምትጠራ ገጠራማ ቀበሌ አንድ ጫካ ውስጥ እንዲሰፍሩ መገደዳቸውን ገልጹአል።
ህጻናት፣ እርጉዝ ሴቶች እና በሽተኞች ሳይቀሩ ቀን በጸሀይ፣  ሌሊት በብርድ እያንዳንዷን ቀን እንዲያስልፉ መገደዳቸውን የገለጠው ዘእጋቢያችን በመጀመሪያው ዙር ተፈናቅለው በባህርዳር ከተማ ከሚገኙት ተፈናቃዮች መካከል አንድ አርሶአደር የክልሉ ባለስልጣናት ጉዳዩ የክልል ስድስት ጉዳይ በመሆኑ ክልል ሶስት አያገባውም የሚል ምላሽ የሰጡአቸው መሆኑ ታውቁአል።

አንድነት በህሊና እስረኞች ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሊጀምር ነው

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አባል የሆነው አቶ ናትናኤል መኮንን ከአንድ ሳምንት በላይ በርሀብ አድማ ላይ እንደሚገኝ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፁ፡፡
በቂሊንጦ ወህኒ ቤት በቅርቡ በተደረገ ስብሰባ ላይ አልሳተፍም በማለቱ ብቻ ለአንድ ወር ከቤተሰቦቹ ጋር እንዳይገናኝ የተከለከለው አቶ ናትናኤል የወህኒ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ከአንድ ሳምንት በላይ በርሀብ አድማ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ ናትናኤል መኮንን ከቤተሰቦቻቸው እንዳይገናኙ መደረጉን በመቃወም የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ወደ ወህኒ ቤት በማምራት ማብራሪያ እንደሚጠይቁና ምክንያቱን እንደሚያጣሩ ፓርቲው ለፍኖተ ነፃነት አስታውቋል፡፡
የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ ለፍኖተ ነፃነት እንደተናገሩት አንባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ዜጎችን ማሰሩ ሳያንስ በወህኒ ቤት ውስጥ የሚያደርሰውን ኢሰብአዊ ድርጊት ፓርቲው ያወግዘዋል፡፡ በተለይም በህሊና እስረኞች ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም ሊወስድ ላሰበው የተቃውሞ እንቅስቃሴ መረጃ ለማሰባሰብ ይረዳው ዘንድ የፓርቲውን ሊቀመንበርና ሁለት ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተ ቡድን አቋቁሟል፡፡ ቡድኑ ከወህኒ ቤቱ የሚያገኙትን መልስ መሰረት አድርጎ ፓርቲው የራሱን እርምጃ ይወስዳል፡፡
በፍኖተ ነፃነት አቶ ናትናኤል ስላሉበት ሁኔታ እንዲያስረዱ የተጠየቁት ባለቤታቸው ወ/ሮ ፍቅርተ…. ከአንድ ሳምንት በላይ አቶ ናትናኤልን እንዳላያቸው ገልፀው፤ “ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የሚላክለትን ምግብ አልተቀበለም፤ ያለበት ሁኔታም አሳስቦኛል” ብለዋል፡፡....ፍኖተ ነፃነት

ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃሊቲዎች ክስ ቀረበባት!

Reeyot-Alemuመምህርት እና ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙትን የአስተዳደር እና የጥበቃ ሰራተኞች ትንቂያለሽ፣ትሰደቢያለሽ እንዲሁም “የምትሰሩትን በሚዲያ እና ድረ ገፆች አጋልጣለሁ” ብለሽ ትዝቺያለሽ በሚል ክስ ቀርቦባት መጋቢት 25 /2005 ዓ.ም ቃሏን መስጠቷ ተሰማ፡፡
ጋዜጠኛይቱ ክሱን አስመልክቶ ቃሏን እንድተሰጥ የተጠየቀቸችው መጋቢት 19 /2005 ዓ.ም ምሽት ከመኝታዋ ተቀስቅሳ የነበረ ቢሆንም ከጠበቃዬ ጋር ሳልነጋገር ምንም የምሰጠው ቃል የለኝም በማለቷ እስከ መጋቢት 25 ሊዘገይላት ችሏል፡፡
ርዮት የተከሰሰችው በፌደራል ታራሚዎች አያያዝ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 139/1999 አንቀፅ 36 መ እና ሠ ላይ በተቀመጠው መሰረት ሲሆን ይህ አንቀፅ “ከባድ የዲሲፒሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ድርጊቶች” ተብሎ የተዘረዘረ ነው፡፡
ርዮት ቅጣቱ ተግባራዊ ከተደረገባት፤
ከአንድ ወር እስከ አራት ወር ለሚደርስ ጊዜ በወዳጅ ዘመዶቿ እንዳትጎበኝ፤ ደብዳቤ እንዳትልክ እና እንዳትቀበል (ይሄ እንኳ አሁንም ተግባራዊ ተደርጎባታል) የእስር ቤቱን ቤተ መጻህፍት እንዳትጠቀም፣ በእስር ቤቱ በሚደረግ የጋራ ዝግጅት እና መዝናኛ ላይ እንዳትሳተፍ እንዲሁም ከአንድ ወር እስከ ሁለት ወር ለሚደርስ ጊዜ ለብቻ እስር ትዳረጋለች፡፡
እንዲህ ከሆነ ደግሞ ያቺ በቃሊቲዊቹ ውቃቢ ትፈቀድ የነበረች አመክሮም ልትከለከል ነው ማለት ነው፡፡
በነገራችን ላይ ወጣቱ ፖለቲከኛ ናትናኤልም በእስር ቤቱ እየደረሰበት ያለውን አበሳ በመቃወም የርሃብ አድማ ላይ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ አባላትም ቅጥ ያጣውን የእስር ስርዓት ሃይ ለማለት የርሃብ አድማ ላይ ናቸው፡፡
ወይ ጣጣ… ብዬ የራሴን አስተያየት በአዲስ መስመር አቀርባለሁ…
እኔ የምለው ግን ኢህአዴግ ምነው እንዲህ መካሪ አጣ…? እርሱ እኛን በስንቱ መከራ እንዳልመከረን እርሱን የሚመክረው ማጣቱ የሚገርም ነው፡፡
እስቲ አሁን በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን እስሩ አንሶ አሳር የሚያበላው ምን ይሁነኝ ብሎ ነው? እንደሰማነው በርካታ የህሊና እስረኞች በታመሙ ጊዜ የሚያክሟቸው የእስር ቤቱ ሀኪሞች “መግደል ነበር አንተን” “መጨረስ ነበር አንቺን” እያሉ ያስፈራራሉ፡፡ እውነቱን ለመናገር ይሄ የመጨረሻው ዘመን ምልክት ነውና ነቅታችሁ ጠብቁ፡፡ መንግስታችን “ባትሪ ሎው” እያለ ይመስለኛል! source Abetokichaw blog.

መንግስት የክልል ነዋሪዎችን በአዲስ አበባ ምርጫ ሊያሳትፍ ነው
መጋቢት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው የአዲስ አበባና የወረዳ ምርጫዎች የተመዘገበው መራጭ ቁጥር ከተጠበቀው በታች መውረዱ ያሰጋው መንግስት ፣ ከክልል ከተሞች የራሱ ደጋፊ አባላትን በማምጣት በምርጫው እንዲሳተፉ ዛሬ ስልጠና ሲሰጥ ውሎአል።

ከክልል የመጡት ሰዎች በተለያዩ ወረዳዎች በሚገኙ የስልጠና ጣቢያዎች በመጪው ምርጫ እንዴት ድምጽ እንደሚሰጡ ስልጠና እየተሰጣቸው ነው። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በነጻነት ትምህርት ቤት 600 ሰልጣኖች ዛሬ ስልጠና የተሰጣቸው ሲሆን፣ አብዛኞቹ ሰልጣኖች ቴክኒካዊ የሆኑ ነገሮችን ሲማሩ መዋላቸውን እና በምርጫው እለት ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ግር እንዳይላቸው አስፈላጊውን የሲሙሌሽን ትምህርት ሲማሩ መዋላቸውን በስልጠናው የተሳተፈ አንድ የድርጅት አባል ለኢሳት ገልጿል።

ዛሬ በተሰጠው ስልጠና ከ5 ሺ ያለነሱ ከየክፍለሀገራቱ ተውጣጠው የመጡ የገዢው ፓርቲ አባላት ተሳትፈዋል። በተከታታይ ዙር ስልጠናዎች ሌሎች አዳዲስ አባል መራጮች እንደሚሳተፉ ለማወቅ ተችሎአል።

ኢህአዴግ ያለማንም ተፎካካሪ ፓርቲ በአዲስ አበባ እንደሚያሸንፍ ቢያውቅም ፣ የመራጩ ቁጥር መቀነስ ፖለቲካዊ ገጽታ ያበላሻል በሚል ስሌት መራጮችን ከክፍለሀገር ማስመጣት ብቻ ሳይሆን፣ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ሳይቀር እንዴት እንደሚመርጡ እያሰለጠነ እንደሚገኝ መዘገባችን ይታወሳል።

33 የፖለቲካ ድርጅቶች ስለመጪው ምርጫ ህገወጥነት ህዝቡን ሊያወያዩ ነው
መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ራሳቸውን ከምርጫው ያገለሉ 33ቱ የአዳማ ፔትሽን ፈራሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በመጪው እሁድ መጋቢት 29 ቀን 2005 ዓም ህዝቡን ለውይይት ጠርተዋል።

ከህዝቡ ጋር የሚደረገው ውይይት በአንድነት ፣ በመድረክ፣ በሰማያዊ እና በመኢአድ ፓርቲዎች አዳራሾች ከ ቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን፣ የስብሰባው አላማም መጪው ምርጫው ህገወጥ መሆኑን ለህዝቡ ለማስረዳት ነው።

በሌላ ዜና ደግሞ በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ አመራሮች ጠበቃ የሆኑት አቶ ተማም አባቡልጉ ፣ በመጪው እሁድ ከቀኑ 3 ሰአት ላይ የሀይማኖት ነጻነትና ህገመንግሰቱ በሚል ጥናታዊ ወረቀት ለህዝቡ እንደሚያቀርቡ ታውቋል።