Tuesday 2 April 2013


የግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ አካል ነዉ፣ በሚል ርእስ መግለጫ ያወጣ ሲሆን በመግለጫው ላይ እንዳሰፈረው ወያኔ በዚህ በያዝነዉ አመት ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ  በአማራዉ ህዝብ ላይ አዲስና ሰፋ ያለ የጥቃት ዘመቻ መጀመሩን አውስቱአል፣  የግንቦት ሰባት ንቅናቄ    በዚሁ መግለጫ ማጠቃለያው ላይ በአማራዉ ብሔረሰብ ላይ በማነጣጠር እየተፈጸመ ያለው የማፈናቀልና  የማጥቃት እርምጃ በአገሪቱም ሆነ በአለም አቀፍ ህጎች ሁሉ  በዘረኝነት ወንጀል የሚያስጠይቅ ከፍተኛ  በደል ነው ብሎአል።
የፕሮግራማችን ተከታታዮች የዚህን መግለጫ ሙሉ ቃል ከዜናው በማስከተል የምናቀርብ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።
ይህ በንዲህ እንዳለ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በፍኖተሰላም እና በባህርዳር ከተማ ያለመጠለያ ተበትነው የሚገኙ የአማራ ተወላጆች፣ ለዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ባደሩ ሆድ አደር ባለስልጣናት አሁንም ግፍና በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ አመለከተ። የግንቦት ሰባት ዘጋቢ ከባህር ዳር ባስተላለፈልን በዚሁ ሪፖርት ላይ እንዳመለከተው እነኝህ ተፈናቃዮች እያቀረቡ ላለው ጥያቄ  የክልል ባለስልጣናት ተብየዎች ምንም አይነት መፍትሄ ሊሰጡአቸው ባለመቻሉ ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውንና ከዚህም አልፎ ከህዝብ እይታ ለመሰወር በሚል ራቅ ወዳለ ቦታ እንዲሰፍሩ መደረጋቸውን  ገለጹአል።
ዘጋቢያችን እንደገለጠው እነኝኝህ በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ሰፍረው የነበሩ ከ3 ሺ በላይ ተፈናቃዮች ከመሀል ከተማ እንዲወጡ ተደርገው፣ ጃቢ ጣህናን ወረዳ ውስጥ ባከል እየባለች በምትጠራ ገጠራማ ቀበሌ አንድ ጫካ ውስጥ እንዲሰፍሩ መገደዳቸውን ገልጹአል።
ህጻናት፣ እርጉዝ ሴቶች እና በሽተኞች ሳይቀሩ ቀን በጸሀይ፣  ሌሊት በብርድ እያንዳንዷን ቀን እንዲያስልፉ መገደዳቸውን የገለጠው ዘእጋቢያችን በመጀመሪያው ዙር ተፈናቅለው በባህርዳር ከተማ ከሚገኙት ተፈናቃዮች መካከል አንድ አርሶአደር የክልሉ ባለስልጣናት ጉዳዩ የክልል ስድስት ጉዳይ በመሆኑ ክልል ሶስት አያገባውም የሚል ምላሽ የሰጡአቸው መሆኑ ታውቁአል።

No comments:

Post a Comment