Tuesday 2 April 2013


33 የፖለቲካ ድርጅቶች ስለመጪው ምርጫ ህገወጥነት ህዝቡን ሊያወያዩ ነው
መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ራሳቸውን ከምርጫው ያገለሉ 33ቱ የአዳማ ፔትሽን ፈራሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በመጪው እሁድ መጋቢት 29 ቀን 2005 ዓም ህዝቡን ለውይይት ጠርተዋል።

ከህዝቡ ጋር የሚደረገው ውይይት በአንድነት ፣ በመድረክ፣ በሰማያዊ እና በመኢአድ ፓርቲዎች አዳራሾች ከ ቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን፣ የስብሰባው አላማም መጪው ምርጫው ህገወጥ መሆኑን ለህዝቡ ለማስረዳት ነው።

በሌላ ዜና ደግሞ በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ አመራሮች ጠበቃ የሆኑት አቶ ተማም አባቡልጉ ፣ በመጪው እሁድ ከቀኑ 3 ሰአት ላይ የሀይማኖት ነጻነትና ህገመንግሰቱ በሚል ጥናታዊ ወረቀት ለህዝቡ እንደሚያቀርቡ ታውቋል።

No comments:

Post a Comment