Tuesday 2 April 2013


ሰበር ዜና) አርቲስት ቲዎድሮስ ካሳሁን ለጊዜው ምንነቱ ባልታወቀ አለመግባባት ምክንያት ከባለቤቱ መፋታቱ ተነገረ

The recently married artist Tewodros Kassahun aka Tedy Afro has reportedly been divorced, sources closer to the artist Told EthiopianObserver. The divorce comes after a continuous argument between the two. According to the sources Amleset Muche has already left him and now she is with her parents. Our effort to reach Tedy Afro via phone is not successful yet. Read More on EthiopianObserver
በቅርቡ ጋብቻቸውን የፈፀሙት አርቲስት ቲዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና ባለቤቱ መፋታታቸው እየተነገረ ነው፡፡ ለአርቲስቱ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ትናንት ምሽት አካባቢ ለኢትዮጵያን ኦብሰርቨር እንደጠቆሙት ጥንዶቹ የተፋቱት ለቀናት በዘለቀ አለግባባት ምክንያት ነው፡፡ ለጊዜው አለመግባባት የተፈጠረበት ምክንያት ግልፅ ባይሆንም ጉዳዩን አጣርተን እንደደረሰን እናቀርባለለን፡፡ የቴዲ ባለቤት በአሁን ሰዓት በቤተሰቦቿ ቤት እንደምትገኝ ተረጋግጧል፡፡
ጉዳዩ እንዲህ ነው
ያለፉት 13 ቀናት ለአርቲስት ቲዎድሮስ ካሳሁን እና ባለቤቱ አምለሰት ሙጬ ጥሩ አልነበሩም፡፡ ቴዲ በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ጮክ ብሎ ማውራት ጀምሯል፡፡ አምለሰት ባሌቤቷ ቅናት ብጤ እንደጀማመረው እርግጠኛ ሆናለች፡፡ ሁኔታው ቢያስቃትም እየተደጋገመ ሲሄድ ግን ትግስቷ ያለቀ ይመስላል፡፡
“ቢያንስ ቀስ ብለህ አውራ ጎረቤት እስኪሰማ ድረስ ለምን ትጮሃለህ” ስትለው እንደነበርም ግድግዳ ተደግፈው ሲያዳምጡ እንደነበር የሚገልፁ የአርቲስቱ ጎረቤቶች ለኢትዮጵያን ኦብዘርቨር ተናግረዋል፡፡ የመረጃ ምንጮቻችን አያይዘውም ቴዲ ሰሞኑን የማንንም ስልክ እያልመለሰ መሆኑን ነው የጠቆሙት፡፡
አርቲስቱ በቅርቡ “ትዳር” የተሰኘ አልበም ለማውጣት በእንቅስቃሴ ላይ ነው ያሉት እንዚሁ ምንጮቻችን አሁን ከተፈጠረው ሁኔታ አንፃር የዘፈኖቹ ይዘት ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም ባይ ናቸው፡፡
ይህን መረጃ እያጠናከርን ባለlበት ሰዓት አርቲስቱ ቤቱን ቆልፎ ከአዲስ አበባ ራቅ ወዳለ ቦታ ሳይሄድ እንዳልቀረም የሚጠቁሙ መረጃዎች እየደረሱን ነው፡፡ ምናልባትም በአሁን ሰዓት አርቲስቱ ራቅ ወዳለ ቦታ የሄደው ለአዲሱ አልበሙ መጠሪያ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀውን “ትዳር” የተሰኘ ዜማ ለመለማመድ ሳይሆን እንደማይቀር ይህን አፕሪል ዘ ፉል አስቀድመው ነቄ ያሉ ሁላ ይደርሱበታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
እወነታው ይሄ ነው፡፡ ቴዲ አፍሮና ና ተወዳጇ ሚስቱ አሁንም ትዳራቸውን በፍቅር እየመሩ ነው፡፡ የአብርሃምና የሳራ እንዲሆንላቸውም እንመኛለን፡፡
Read More on EthiopianObserver
source freedom4Ethiopian

No comments:

Post a Comment