Saturday 30 March 2013

በሳኡዲአረቢያ ሊያኖረው የሚችል ፈቃድ ስለሌለው ብቻ ረቡእ ማታ 1 ወጣት አውራሪስ ተሾመ ከለሊቱ አምስት ሰአት ገደማ በአረቦች ተገደለ ::

በሳኡዲ አረቢያ በአቋራጭ ጎዳና በመሰደድ አስከፊ ህይወታቸውን ለመታደግ ብሎም ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት ደፋ ቀና እያሉ ከአገራቸው ዳር ድንበር እየተሰደዱ የሚገኙት ወጣቶች ከፍተኛ ስቃይ እና እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን የደረሰን ዜና ዘገባ
ያመለክታል ።
በዚህ ባሳለፍነው ረቡእ ማታ ከለሊቱ አምስት ሰአት ገደማ በአረቦች ተገደለ የተባለው ወጣት ።በሳኡዲአረቢያ ሊያኖረው የሚችል ፈቃድ ስለሌለው ብቻ እንዲገደል ማድረጋቸውን እና አስከሬኑ ወደ ሃገሩ ይላክ ሲባልም ህገወት የገባ ስደተና ስለሆነ ልንሰጣችሁ አንችልም በማለት ምላሽ መስጠታቸውን ከስፍራው ያነጋገርናቸው ወገኖቻችን ገልጸዋል ። እንደ ህበረተሰቡ አገላለስ ከሆነ ልጁን እኛ አልገደልነውም እያሉ ይዋሹናል የገደለው መብረቅ ነው ብለው እያሉ እኛንም እያስፈራሩን ይገኛሉ ሲሉ ተናግረዋል ።

የተገደለው ልጅ ስሙ ወጣት አውራሪስ ተሾመ የሚባል ሲሆን ትውልዱም በሰሜን ሸዋ ክፍለ ሃገር በኤፍራታና ጅሌ ወረዳ የካራቆሬ ከተማ ተወላጅ እንደሆነ ካገኙት የመታወቂያ መረጃ ለማወቅ ተችሎአል ።የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል በአሁን ሰአት በጂዳ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ለማነጋገር እና የዚህን ሟች አስከሬን ወደ ትውልድ አገሩ የሚላክበት ዘዴ ይፈጥር ዘንድ ትረት በማድረግ ላይ እንገኛለን ።
እንዲህ አይነቱ ችግር ሲፈጠር ማናቸውም ግለሰቦችም ቢሆኑ በግላቸው ጥረት በማድረግ አስፈላጊውን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ እንዳይታቀቡ የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ያሳስባል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን በአረብ አገር ላይ እየተሰደዱ በሚገኙት ወጣቶች ላይ የድብደባ እና ግድያ ወንጀል መበራከቱን ባሳለፍነው ሳምንታት ያቀረብናቸው የምስል ቅንብሮች ማስታወስ የሚቻል ነው ። ማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ለወላጅ ቤተሰቦቹ መጥናናትን እየተመኘ ለእልፈተ ህይወቱም የሰላም እረፍት ነፍስን በገነት ያኑርልን ይላሉ ።source 
Minilik Salsawi
በሳኡዲአረቢያ ሊያኖረው የሚችል ፈቃድ ስለሌለው ብቻ ረቡእ ማታ 1 ወጣት አውራሪስ ተሾመ ከለሊቱ አምስት ሰአት ገደማ በአረቦች ተገደለ ::

በሳኡዲ አረቢያ በአቋራጭ ጎዳና በመሰደድ አስከፊ ህይወታቸውን ለመታደግ ብሎም ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት ደፋ ቀና እያሉ ከአገራቸው ዳር ድንበር እየተሰደዱ የሚገኙት ወጣቶች ከፍተኛ ስቃይ እና እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን የደረሰን ዜና ዘገባ 
ያመለክታል ። 
በዚህ ባሳለፍነው ረቡእ ማታ ከለሊቱ አምስት ሰአት ገደማ በአረቦች ተገደለ የተባለው ወጣት ።በሳኡዲአረቢያ ሊያኖረው የሚችል ፈቃድ ስለሌለው ብቻ እንዲገደል ማድረጋቸውን እና አስከሬኑ ወደ ሃገሩ ይላክ ሲባልም ህገወት የገባ ስደተና ስለሆነ ልንሰጣችሁ አንችልም በማለት ምላሽ መስጠታቸውን ከስፍራው ያነጋገርናቸው ወገኖቻችን ገልጸዋል ። እንደ ህበረተሰቡ አገላለስ ከሆነ ልጁን እኛ አልገደልነውም እያሉ ይዋሹናል የገደለው መብረቅ ነው ብለው እያሉ እኛንም እያስፈራሩን ይገኛሉ ሲሉ ተናግረዋል ።

የተገደለው ልጅ ስሙ ወጣት አውራሪስ ተሾመ የሚባል ሲሆን ትውልዱም በሰሜን ሸዋ ክፍለ ሃገር በኤፍራታና ጅሌ ወረዳ የካራቆሬ ከተማ ተወላጅ እንደሆነ ካገኙት የመታወቂያ መረጃ ለማወቅ ተችሎአል ።የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል በአሁን ሰአት በጂዳ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ለማነጋገር እና የዚህን ሟች አስከሬን ወደ ትውልድ አገሩ የሚላክበት ዘዴ ይፈጥር ዘንድ ትረት በማድረግ ላይ እንገኛለን ።
 እንዲህ አይነቱ ችግር ሲፈጠር ማናቸውም ግለሰቦችም ቢሆኑ በግላቸው ጥረት በማድረግ አስፈላጊውን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ እንዳይታቀቡ የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ያሳስባል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን በአረብ አገር ላይ እየተሰደዱ በሚገኙት ወጣቶች ላይ የድብደባ እና ግድያ ወንጀል መበራከቱን ባሳለፍነው ሳምንታት ያቀረብናቸው የምስል ቅንብሮች ማስታወስ የሚቻል ነው ። ማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ለወላጅ ቤተሰቦቹ መጥናናትን እየተመኘ ለእልፈተ ህይወቱም የሰላም እረፍት ነፍስን በገነት ያኑርልን ይላሉ ።

No comments:

Post a Comment