Sunday 31 March 2013


እሥራኤል በሜዴትራኒያን ጠረፏ አኳያ ከሚገኝ የታማር ምድር የተፈጥሮ ጋዝ ማውጣት ጀመረች። የአገሪቱ የኤነርጂና የውሃ ሃብት ሚኒስትር ተቋም እንዳስታወቀው ጥሬው ጋዝ ለማጣራት ተግባር አሽዶድ ወደተሰኘችው ስፍራ እንዲተላለፍ ተደርጓል። ታማር ምድር የሚገኘው ከሃይፋ ወደብ 80 ኪሎሜትር ራቅ ብሎ ሜዴትራኒያን ባሕር ውስጥ ነው። ስፍራው 238 ሚሊያርድ ሜትር-ኩብ የሚደርስ  የጋዝ ክምችት እንዳለው የሚገመት ሲሆን የሚወጣውም በእሥራኤልና በአሜሪካ ኩባንያዎች ትብብር ነው። እሥራኤል በምርቱ መውጣት በውጭ ከነበራት ጥገኝነት እንደምትላቀቅ ተነግሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የጋዝ ማውጣቱ ተግባር የተጀመረበትን ዕለት ለእሥራኤል ኤኮኖሚ ታላቅ ቀን ነው ብለውታል። source DW.

No comments:

Post a Comment