Sunday 24 March 2013

! …… የመረጃ ዴሞክራሲ: ለተሻለ ለውጥ …..!

ትናንት “የትግራይ ህዝብ እየተጨቆነ ዝምታን የመረጠበት ምክንያት በትግራይ የመረጃ ዓፈና ስላለ ኣብዛኛው ሰው የህወሓትን የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ለማመን ስለሚገደድ ተቃዋሚዎች ወደ ህዝቡ ቀርበው ፖሊስዎቻቸውና ለትግራይ ህዝብ ያላቸው ግምት ቢያስረዱና መግባባት ቢችሉ መልካም ነው።” የሚል መልእክት ያለው ፅሑፍ ኣስፍሬ ነበር።

ከዚህ በመነሳት ከተነሱ ጥያቄዎች ሁለቱን ልመልስ፣

(1) “የትግራይን ህዝብ የተባለውን ሁሉ ይቀበላል እያልክ ነው? ማገናዘብ የሚችል ጭንቅላት የለውም እያልክ ነው? ይሄ ስድብ ነው። በጣም ተሳስተሃል።” Edy Berhane.

(2) “ተቃዋሚዎችን መጋበዝ ህ ከእውነት እንድትርቅ እያረገህ ነው። ተቃዋሚዎች ኮ ኣማራጭ ፖሊሲ የላቸውም። ህዝብን ከመሳደብ ውጭ ኣማራጭ ሲያቀርቡ ኣላየንም።” Alema Dola Sangade.

መልስ

(1) “የትግራይ ህዝብ የመረጃ ዓፈና ስለሚደርሰው የፕሮፓጋንዳ ሰለባ እየሆነ ነው”; ማለት ህዝብን መሳደብ ኣይደለም። ማገናዘብ??? ማገናዘብ ኮ የሚቻለው እውቀቱ ሲኖረን ነው። የእውቀት መሰረቱ ደግሞ መረጃ ነው። መረጃ ሲኖረን ነው ኣመዛዝነን የሚጠቅመንና የሚጎዳን ለመየትና መወሰን የምንችለው። ትክክለኛና በቂ መረጃ (ስለ ኣንድ ጉዳይ) ከሌለን የማመዛዘን ዕድላችን ሊበላሽ ይችላል።

ተራ ገበሬዎች ወይ ነጋዴዎች ወይ ሌሎች ይቅርና በጣም የተማሩ ወይ ልምድ ያላቸው የፍርድቤት ዳኞች እንኳ በቂና ትክክለኛ መረጃ (ከሁለቱም ወገኖች) ካላገኙ ሚዛናዊና ትክክለኛ ፍርድ (ውሳኔ) ላይሰጡ ይችላሉ (ጭንቅላታቸው ማገናዘብ ወይ ማመዛዘን ስለማይችል ሳይሆን በመረጃ ችግር ወይ እጥረት ማለት ነው)። የመረጃ ማነስ ውሳኔዎቻችንን ሊያበላሽ ይችላል። ስለዚ ህዝብን ኣልተሳደብኩም። ለፖለቲካዊ ፍጆታ ብቻ ሲባል ‘ህዝብ (መረጃ ሳይኖረውም) ማገናዘብ ይችላል’ ብለን ከደመደምን ግን ግብዝነት ነው የሚሆነው።

እንደኔ እንደኔ ግን ‘ህዝብ የሚያገናዝብ ጭንቅላት የለውም’ ብሎ የህዝብን የማገናዘብ ዓቅም ኣሳንሶ እያየ ያለው ገዢው ፓርቲ ይመስለኛል። መረጃ የማፈን ዓላማና ኣንድምታው ምንድነው? ለህዝብ ፍላጎት መቆም ያለበት መንግስት እንዴት የህዝብን መረጃ የማግኘት መብት ይገድባል? ባለስልጣኖቻችን እኛ (ህዝብ) ምን ዓይነት መረጃ እንደሚያስፈልገን (ወይ እንደማያስፈልገን) ሊወስንሉን ኣይገባቸውም ነበር። ህዝቡ ሁሉም ዓይነት መረጃ እንዲያገኝ ይፈቀድለት፤ ከዛ የሚጠቅመውና የሚጎዳው ለይቶ መወሰንና መምረጥ ይችላል (ማገናዘብ የሚችል ህሊና ኣለውና)።

የመንግስት ኣካላት በህዝቡ ፍላጎት ጣልቃ ገብተው፣ የመረጃ ነፃነቱን ገድበው የሚጠቅመውና የማይጠቅመው (በራሳቸው ፍላጎት መሰረት) ወስነው ካቀረቡለት (ሌሎችን ትቶ ኢቲቪ ብቻ እንዲከታተል ከፈረዱበት) ኣንድም ‘ህዝብ ማገናዘብ የሚችል ህሊና የለውም’ እያሉን ነው ኣልያም ደግሞ የህዝብን የመረጃ መብት በማፈን ለህዝብ ያላቸውን ንቀት እያሳዩን ነው።

(2) ተቃዋሚዎች ከህዝብ እንዲግባቡ መጋበዝ ኣማራጭ ፖሊሲ እንዳላቸው መጠቆም ወይ ኣለመጥቆም ኣያሳይም። የሚያሳየው ነገር ቢኖር በዲሞክራሲያዊ መርህ የፖለቲካ ድርጅቶች ከህዝብ ጋር መገናኘት ኣለባቸው። ሓሳባቸው ለህዝብ ያቅርቡ። ኣማራጭ ፖሊሲ ኣላቸው ወይስ የላቸውም? ካላቸውስ ከገዢው ፓርቲ ፖሊሲ ይሻላል ወይስ ኣይሻልም ??? ወዘተረፈ … መወሰን ያለበት ህዝቡ ነው። የኔ ነጥብ; ህዝቡ ሁሉም ኣማራጮች ቀርበውለት (መረጃ የማግኘት መብቱ ተጠብቆ) በራሱ ህሊና ይፍረድ የሚል ነው። ስልጣን የህዝብ ይሁን ነው።

ተቃዋሚዎች ኣማራጭ ፖሊሲ ከሌላቸው “የላችሁምና ኣንመርጣችሁም” ብሎ ሊላቸው የሚገባ ህዝቡ ራሱ እንጂ ገዢው ፓርቲ (መረጃ በማፈን … ተቃዋሚዎች ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙ በማድረግ) ኣይደለም።

ተቃዋሚዎች (ፖሊሲ ቢኖራቸውም ባይኖራቸውም) ኣማራጭ ድርጅት (ፓርቲዎቹ ራሳቸው) ማቋቋማቸው በራሱ ለሕብረተሰብ ትልቅ ጠቀሜታ ኣለው። ምክንያቱ የኣንድ የፖለቲካ ፓርቲ ዓላማ የመንግስትነት ስልጣን ይዞ የሀገር ልማት ማፋጠን ነው። በኢትዮዽያ ታሪክ (እስከ ኣሁን ድረስ) ስልጣን የተያዘው በህዝብ ፍላጎትና ምርጫ ሳይሆን በጠመንጃ ኣፈሙዝ ነው።

ፓርቲዎች ተጠናክረው ስልጣን መያዝ ከቻሉ ታድያ ለመጀመርያ ግዜ ሰለማዊ የስልጣን ሽግ ግር ተግባራዊ ያደርጋሉ። (የኢትዮዽያ የፖለቲካ ታሪክ ይቀይራሉ) ሰለማዊ ሽግግር ተደረገ ማለት ደግሞ ስልጣን ወደ ህዝብ ወረደ ማለት ነው። ህዝብ የስልጣን ባለቤት ከሆነ የመንግስት ኣካላት የሰው ጌቶች ሳይሆኑ የሰው ኣገልጋዮች ሆኑ ማለት ነው። በዚህ መልኩ የህዝቦች ነፃነት ተከበረ ማለት ነው፤ ቀጥሎም እኩልነት፣ ኣንድነት፣ መከባበር ይኖራሉ። እኛም ተዋደድን። ስለዚ ፓርቲዎች ሊከበሩ ይገባል።

ከወራት በፊት ተመሳሳይ ጥያቄ ደርሶኝ ነው። የሰጠሁት መልስ እንዲህ ነው:

“In order to achieve human freedom, we need democracy. The people must be the source of state power. They should be allowed to elect their representatives freely.

Election is choice. Choice must be rational, which entails that there must at least be two or more alternatives. Political parties must be allowed to organize themselves and conduct campaigns to announce their policies. The people should have relatively full information about the alternative programs of the contending parties.

For the information dissemination, independent media should exist. This leads to free competition. To make the competition fair, there must be an independent judiciary, independent safeguarding machinery (military, police, court ...) and electoral board. The vote must be respected and the party with the highest vote must hold the government.

This is the Olympics of politics. The process of the competition to assume state power must be clear and transparent so that people also participate in following the game. In the Olympics of athletics, for example, the people (the spectators) also observe and judge the game, because it is transparent.

Had some of the athletes been allowed to use guns (pistols), we would have never achieved such amazing performance. Same rules and regulations must apply to political games too, (though highly ideal). Guns (bullets) should not be used in the elections (political games).

Those with brilliant ideas that can benefit the society must win.”



It is so!!!
by 

Abraha Desta

No comments:

Post a Comment