Friday 29 March 2013

መንግስት ለአባይ ግድብ ግንባታ ከህዝብ ለመሰብሰብ ያወጣውን እቅድ ሳይተወው አይቀርም ተባለ

መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት የአባይ ግድብን በሕዝብ ተሳትፎ ለመገንባት ባቀደው መሰረት ከመንግስት ሰራተኞች፣ባለሃብቶች፣አርሶአደሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች እያካሄደ ያለውን የገንዘብ ማሰባሰብ ሒደት ዘንድሮም ለመቀጠልም አቅዶ ቢንቀሳቀስም ከህዝቡ የታሰበውን ያህል ምላሽ ባለመገኘቱ ለማቋረጥ ሳይገደድ እንደማይቀር ምንጮቻችን ገለጡ።

የአባይ ግድብ ከተጀመረ በኋላ በተለይ ባለፈው ዓመት የመንግስት ሰራተኞች ሳይወዱ በግድ የአንድ ወር እና ከዚያ በላይ ደመወዛቸውን በአንድ ዓመት ከፍለው ለመጨረስ ቃል እንዲገቡ በማድረግ ገንዘብ ለማሰባሰብ መሞከሩ የሚታወስ ሲሆን፣ መዋጮው ስጦታ መሆኑ ቀርቶ በቦንድ ግዥ እንደሚያዝ፣ይህም የቁጠባ ባህልን ለማበረታታት ጥሩ አጋጣሚ መሆኑን በመጥቀስ መንግስት ዘንድሮም መዋጮ ለማሰባሰብ ሙከራ ያደረገ ቢሆንም ምላ ሹ ጥሩ ባለመሆኑ ምክንያት ለማቋረጥ ሳይገደድ አይቀርም።

ለዚህ አንዱና ዋንኛው ምክንያት ከዋጋ ንረት ጋር ተያይዞ ደመወዝተኛው በገቢው ለመተዳደር ያለመቻል ሲሆን በተጨማሪም ለፕሮጀክቱ ከሕዝብ በመዋጮ መልክ የሚሰበሰበው ገንዘብ በምን መልኩ ስራ ላይ እየዋለ እንደሆነ፣ከሙስናና ብልሹ አሰራር የጸዳ ስለመሆኑ ምንም ዓይነት ግልጽ መረጃ አለመኖሩ በሕዝብ ውስጥ ጥርጣሬን ፈጥሯል፡፡ ሌላው ቀርቶ ስንት ብር እንደተዋጣ እንኳን መንግስት ተከታታይነት ያለው በቂ መረጃ እየሰጠ አለመሆኑ የበርካታ ወገኖችን ቅሬታ አስከትሏል፡፡

ለግድቡ ገንዘብ ለመስጠት ቃል የገቡ ሼህ አላሙዲንን ጨምሮ በርካታ ባለሃብቶችም ገንዘቡን በወቅቱ ገቢ አለማድረጋቸው በእነአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝና አቶ በረከት ስምኦን የሚመራውን የአባይ ግድብ ብሔራዊ ም/ቤትና አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናትን ማበሳጨቱ ታውቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከመጋቢት 18 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ግድቡ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት ሁለተኛ ዓመት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment