Wednesday 27 March 2013


የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና የአንድነት ለዴሞክራሲና ፍትኅ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባል፤ የአቶ አንዱዓለም አራጌ የይግባኝ  ውሳኔ በተለዋጭ ቀጠሮ መጋቢት 30 እንዲታይ ፍርድ ቤት መወሰኑን AFP ዜና አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።  እስክንድር ነጋ፤ አቶ አንዱዓለም አራጌና ባጠቃላይ 24 ኢትዮጵያውያን  አምና በሐምሌ  ፀረ ሽብር ህግ ጥሰዋል ያለው ፍርድ ቤት እስራት እንደበየነባቸው የሚታወስ ነው። AFP እንደጠቀሰው፤ 2 ቱ ተከሳሾች፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ህገ-ወጥ አድርጎ ከሚመለከተው ግንቦት 7 ከተሰኘው ድርጅት ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለውም ነው ክስ የቀረበባቸው። የአቶ አንዱዓለም ጠበቃ አቶ ደርበው ተመሥገን፤ ዳኞች ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጡት፤ መረጃዎችን ለመመርመር ጊዜ ያስፈልገናል በማለታቸው ነው ሲሉ አስረድተዋል። እስክንድር ለ 18 ዓመት አቶ አንዱዓለም ደግሞ ዕድሜ ይፍታኅ የተበየነባቸው መሆኑ የታወቀ ነው። ሁለቱም ፤ በዛሬው ዕለት ፍርድ  ቤት እንዳልቀረቡ የዜናው አገልግሎት ጨምሮ  ገልጿል።
የኢትዮጵያውን ጸረ ሽብር ህግ፣ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፤ በግልጽ ያልተቀመጠ ነው ከማለታቸውም፤ መንግሥት፣ ህጉን ሰላማዊ ተቃውሞን ለማረቅ ይጠቀምበታል ሲሉ መንቀፋቸው ይጠቀሳል።....http://www.dw.de 

No comments:

Post a Comment