Sunday 31 March 2013

ሲዋን - ዳንኤል ገዛኸኝ

ጋዜጠኛ ዳንኤል ገዛኸኝ ከ1997ቱ የኢትዮጵያ ምርጫ በኋላ “በመንግሥት ኃይሎች ደረሰብኝ” በሚለው እሥራት፣ ወከባ፣ ድብደባና በቅልብ ውሻ የመነከስ ጥቃት በታኅሣስ 1998 ዓ.ም ለመሰደድ በቅቷል፡፡
ሲዋን - በዳንኤል ገዛኸኝ
ሲዋን - በዳንኤል ገዛኸኝ
ዳንኤል ገዛኸኝዳንኤል ገዛኸኝ
​​ዳንኤል ገዛኸኝ ከ1997ቱ የኢትዮጵያ ምርጫ በፊት የ“ሞገድ” ጋዜጣ አዘጋጅ እንደነበረ፣ ከዚያ ቀደም ብሎ “ገመና” የተሰኘው በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ጋዜጣ በዋና አዘጋጅነት እንዳገለገለ፣ “ሲዋን” በሚል ርዕስ ባለፈው ዓመት ታትሞ በወጣው መፅሐፉ ሽፋን ላይ ይነበባል፡፡

ጋዜጠኛው ከምርጫው በኋላ “በመንግሥት ኃይሎች ደረሰብኝ” በሚለው እሥራት፣ ወከባ፣ ድብደባና በቅልብ ውሻ የመነከስ ጥቃት በታኅሣስ 1998 ዓ.ም ለመሰደድ በቅቷል፡፡

“ሲዋን” በእብራይስጥ ቋንቋ “ግንቦት” ማለት ነው፡፡

“ሲዋን” ዳንኤል ገዛኸኝ ከአዲስ አበባ አውቶቡስ ተራ ተነስቶ እስከ ሰንዐ - የመን ያሣለፈውን ከባድና ጠመዝማዛ የስደት ጉዞ ይዘግባል፡፡

ዳንኤል ዛሬ በዩናዩትድ ስቴትሷ ጆርጅያ ግዛት የአትላንታ ከተማ ነዋሪ ነው፡፡

ለጥያቄዎችዎ መልስ ይሰጣል፡፡..... http://amharic.voanews.com/content/siwan-by-daniel-gezahagn/1632179.html

No comments:

Post a Comment